09 / ክፍት የሥራ ቦታዎች — የአባላት አገልግሎት
Member services Officer I
ስለ ሥራው ዝርዝር
የዊዝደም ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር ብቁ፣ ተነሳሽነት ያላቸው እና በሙያቸው የላቁ አዲስ ተመራቂዎችን በሚከተለው ክፍት የሥራ ቦታ ላይ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። የሥራ መደብ ዝርዝር • የሥራ መደብ: የአባላት አገልግሎት ኦፊሰር- I (Member Services Officer I) • የቅጥር ሁኔታ: ቋሚ • የሰው ኃይል ፍላጎት: 06 • የሥራ ቦታ: ሀዋሳ • ደመወዝ: በድርጅቱ ስኬል መሰረት መስፈርቶች 1. የትምህርት ደረጃ: ከታወቀ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ (Bachelor's Degree) በሚከተሉት የትምህርት መስኮች የተመረቁ፡- • አካውንቲንግ እና ፋይናንስ (Accounting and Finance) • አካውንቲንግ (Accounting) • ቢዝነስ ማኔጅመንት (Business Management) • ማኔጅመንት (Management) • የህዝብ አስተዳደር (Public Administration) • ሰው ኃይል አስተዳደር (Human Resource Management) • ማኔጅመንት ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ (MIS) • ኢንፎርሜሽን ሲስተምስ (IS) • ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (IT) • ኮምፒውተር ሳይንስ (Computer Science) 2. የሥራ ልምድ: • ዜሮ (0) ዓመት የሥራ ልምድ አዲስ ተመራቂዎች (የ2017 ወይም የ2018)። 3. ሌሎች ክህሎቶች: • ቀልጣፋ የኮሙዩኒኬሽን እና የሰዎች ግንኙነት ክህሎት። • በማይክሮሶፍት ኦፊስ (Word, Excel, PowerPoint) እና የኢንተርኔት አጠቃቀም ክህሎት። • በግል እና በቡድን የመስራት ብቃት። • ጠንካራ ስነ-ምግባር፣ ታማኝነት እና ከፍተኛ የሥራ ተነሳሽነት። ተመራጭ ሁኔታዎች: ከላይ ከተጠቀሱት የትምህርት መስኮች በተጨማሪ፤ በኮምፒውተር አፕሊኬሽን፣ በደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ፣ በዲጂታል ክህሎት ወይም በሌሎች ተዛማጅ የሙያ ስልጠናዎች ሰርተፊኬት ያላቸው ቢኖሩ ቅድሚያ ይሰጣል። የማመልከቻ ጊዜ: ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የትምህርት ማስረጃችሁን፣ ዝርዝር የሥራ ልምድ መግለጫችሁን (CV) እና አፕሊኬሽን ደብዳቤ በመያዝ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ። የማመልከቻ ቦታ: ሀዋሳ፣ የዊዝደም ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማህበር አቶቴ ቅርንጫፍ- ናኖ ቡና መገኛ ህንጻ
መስፈርቶች
- የሥራ መደብ: የአባላት አገልግሎት ኦፊሰር- I (Member Services Officer I)
- የቅጥር ሁኔታ: ቋሚ
- የሰው ኃይል ፍላጎት: 06
- የሥራ ቦታ: ሀዋሳ
- ደመወዝ: በድርጅቱ ስኬል መሰረት
- የትምህርት ደረጃ: በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ አካውንቲንግ፣ ቢዝነስ ማኔጅመንት፣ ማኔጅመንት፣ የህዝብ አስተዳደር፣ ሰው ኃይል አስተዳደር፣ MIS፣ IS፣ IT፣ ኮምፒውተር ሳይንስ ወይም ተዛማጅ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ።
- የሥራ ልምድ: ዜሮ (0) ዓመት የሥራ ልምድ አዲስ ተመራቂዎች (የ2017 ወይም የ2018)።
ለዚህ የሥራ ቦታ ያመልክቱ
ዝርዝር መረጃዎንና ሲቪዎን ይላኩ። የቅጥር ቡድኑ ያገኝዎታል።
ይህ የማመልከቻ መልእክት ወደ ዊዝደም የተዘጋጀ ሆኖ የኢሜይል መተግበሪያዎን ይከፍታል። እባክዎ በማመልከቻ ኢሜይልዎ ውስጥ ሚስጥራዊ የፋይናንስ መረጃ አያካትቱ።
የሥራው ዝርዝር መረጃ
- የሥራ ክፍል
- የአባላት አገልግሎት
- የሥራ ቦታ
- ሀዋሳ
- የሥራ ዓይነት
- ቋሚ
- የወጣበት ቀን
- 19 Oct 2026
- የማመልከቻ ማብቂያ ቀን
- 30 Oct 2026
የቅጥር / የምልመላ ሂደት
ዊዝደም ማመልከቻዎችን በጥንቃቄ በመገምገም ለቀጣይ ምልመላ የተመረጡትን እጩዎች በቀጥታ ያነጋግራል። የምልመላ ሂደቱም የተቋሙን ኦፊሴላዊ መመሪያ ይከተላል።

